# | amh | ara |
---|
1 | ኢራን፤ እንደወንድ እየሆንክ፣ እንደሴት ልበስ | إيران: تصرف كالرجال والبس كالنساء! |
2 | ቀይ ቀሚስ ሻርፕ እና ዓይነ እርግብ ያደረገ አንድ ሰው በማሪቫን ከተማ መንገዶች ኩርዲስታን ግዛት ኢራን ውስጥ በፀጥታ አካላት እየታጀበ እንዲጓዝ ተደረገ፡፡ በቤት ውስጥ ፀብ ምክንያት ጥፋተኛ የተባሉ ሦስት ሰዎች በከተማው መሐል የሴት ቀሚስ አድርገው እንዲጓዙ የግዛቲቱ ፍርድ ቤት ፈርዶባቸዋል፡፡ የቅጣቱ ዓይነት ለብዙዎች ግልጽ ባይሆንም በርካቶች ግን በቅጣቱ እንዲቆጡ አነሳስቷል፡፡ | موكب من قوات الأمن يرافق رجلاً يرتدي فستاناً أحمر وحجاباً يغطي رأسه ويجوب في شوارع مدينة مريوان التابعة لمقاطعة كردستان في إيران في يوم الاثنين ١٥ إبريل/ نيسان ٢٠١۳. حسب قرار محمكة محلية ارتأت أن هذا هو العقاب المناسب لثلاثة رجال تمت إدانتهم بتهمة الإزعاج المنزلي، لم يتم توضيح الظروف الفعلية ولكن فكرة هذا النوع من العقاب أثارت غضب الكثيرين. |
3 | ማክስኞ ዕለት የዓይነ እርግብ ያደረጉ ሴቶች በማርቫን ከተማ ቅጣቱ ቀጪውን ከማስተማር ይልቅ ሴቶችን የሚያዋርድ ነው ሲሉ ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ እንደ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች የፀጥታ አካላት ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ላይ አካላዊ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል፡፡ | قامت النساء في مريوان بعمل مظاهرة ضد هذا الحكم يوم الثلاثاء بحجة أن ذلك أكثر إهانة للنساء منه للرجال المحكومين. وفقا لناشط في حقوق الإنسان فقد قامت قوات الأمن بمهاجمة المتظاهرات بدنياً [بالفارسية]. |
4 | Shared on the Facebook page ‘Kurd Men For Equality' | الڤيديو يُظهر النساء خلال المسيرة. تمت مشاركتها على صفحة ” الرجال الأكراد للمساواة” على فيسبوك |
5 | | على الإنترنت قام كثير من الرجال الأكراد بنشر صورهم وهم يرتدون زياً نسائياً من خلال حملة على فيسبوك تحت شعار “أن تكون امرأة ليس وسيلة للعقاب أو الإهانة”. |
6 | በፌስቡክ በተደረገ የተቃውሞ ዘመቻ ኩርድያዊ ወንዶች ቀሚስ ለብሰው ራሳቸውን ፎቶ በማንሳት በፌስቡክ ገጾቻቸው ለጥፈዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፡- | توجد الصور على صفحة على موقع فيسبوك رجال أكراد للمساواة. كتب نامو كردستاني: |
7 | ‘ሴት መሆን ለቅጣት መሳሪያ መሆንና እና ለማዋረጃ ማስተማሪያ አይደለም' ከላይ የሚታየው ፎቶ የኩርድ ወንዶች ለዕኩልነት የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ ናሞ ኩርዲስታኒ እንዲህ ጽፏል፡- | أنا أريد أن أظهر تضامني ودعمي لفكرة “النسوية” والنساء ومعاناتهن والآلام التي تحملنها على مر العصور والتي سببها لهن “الرجال” في معظم الأحيان. |
8 | ይህ ለሴትነት ያለኝን አጋርነት የማሳይበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ሴቶች በታሪክ በርካታ ችግሮች እና እንግልቶች በወንዶች አማካኝነት እንዲጋፈጡ ሆነዋል፡፡ በቅርቡ እንደተጋፈጥነው እውነታ ደደብ ዳኛ የሴቶችን ልብስ መልበስ እንደ ቅጣት አድርጎ ውሳኔ ሰጥቷል፤ ስለዚህ ይህ ወቅት ሁላችንም በአንድነት በመቆም ይህንን የደደቦች ኢሰብኣዊና ግማሽ የኅብረተሰብ አካላትና በመሬት ላይ የሚኖሩ ግማሽ ድርሻ ያላቸውን ሴቶች የሚያንቋሽሽ ተግባር የመቃወሚያ ወቅት ነው፡፡ እኔ ማድረግ በምችለው ትንሹን ሴትነትን በመደገፍ እፈጽማለሁ፡፡ | سمعنا مؤخراً عن هذا الحكم الغبي من أحد القضاة الذي قرر أن يعاقب شخصاً بجعله يرتدي زياً نسائياً، علينا أن نجتمع سويا ونشجب هذا الغباء والوحشية وعدم الإنسانية ضد النساء؛ اللائي يشكلن نصف المجتمع كما يشكلن نصف الإنسانية على وجه الأرض. أنا أدعم النسوية بأقل شيء أستطيع فعله لهن.. |
9 | የማሪቫን ሴቶች ማህበር በበኩሉ በፌስቡክ ገፁ ድርጊቱን አውግዞ ጽፏል[fa]፡- | على فيسبوك أدانت صفحة اتحاد نساء مريوان هذا الفعل وكتبت [بالفارسية]: |
10 | የፀጥታ አካላት የማሪቫን ከተማ ፍርደኛ ግለሰብን ክብር አዋርደዋል፡፡ እንደሴት አልብሰው በድርጊቱ ክብሩን እንዲያጣ ተመኝተዋል፡፡ የማሪቫን ሴቶች ማኅበር ይህንን ድርጊት ይቃወማል፡፡ እንዲሁም ድርጊቱ ሴቶችን የሚዘልፍ ነው፡፡ የኩርድሽ ሴቶች [ድርጊቱ ከተፈጸመ አንድ ቀን በኋላ] ተቃውመውታል፡፡ | قامت قوات الأمن بجر رجل مُدان من مريوان خلال شوارع المدينة وألبسوه زياً نسائياً على أمل أن يشعر بالإهانة، اتحاد نساء ماريڤان يشجب هذا الفعل ويعتبره إهانة للنساء. قامت النساء الكرديات بالتظاهر ضد هذا الفعل [في اليوم التالي مباشرة]. |
11 | ኢራናዊው ጠበቃ እና የሰብኣዊ መብት ተሟጋች መሐመድ ሙስጠፋ እንዲህ ብሏል[fa]፡- | محمد مصطفاي، محامٍ إيراني ومدافع عن حقوق الإنسان يقول [بالفارسية]: |
12 | የኢራን ሕግ አስፈፃሚ ይህንን የሰው ክብር የሚያዋርድ ድርጊት እንዲፈፅም የሚያስችል የሕግ ከለላ የለውም፡፡ እንደሴት መልበስን ቅጣት የሚያደርግ የኢስላሚክ ሪፖብሊክ ሕግ የለም፡ | القضاء الإيراني ليس لديه الأحقية بأن يقضي عقابا كهذا الذي يأتي ضد الكرامة الإنسانية، أن تجعل الرجل يلبس زياً نسائياً ليس بشئ تجده في قوانين جمهورية إسلامية. |
13 | ታሪክ ራሱን ደገመ | التاريخ يعيد نفسه |
14 | ከሦስት ዓመታት በፊት የኢራን ባለሥልጣናት በተማሪ አራማጆች ላይ ተመሳሳይ የማዋረድ ሥራ ሊሠሩ ሞክረው ነበር፤ አልተሳካላቸውም እንጂ፡፡ | قبل ثلاثة أعوام من الآن حاولت السلطات الإيرانية أن تفعل الشيء نفسه مع طالب ناشط ولكنها فشلت. |
15 | ያን ጊዜ የኢራን ባለሥልጣናት የጠየቁት ማጅድ ሳቫሊን ቴህራን ላይ ንግግር ካደረገ በኋላ በተማሪዎች ቀን እንደሴት እንዲለብስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በኢራን የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች የዓይን ምስክር ጠቅሰው ሪፖርት አወጡ፡፡ ‹‹በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የሚወጡ ማንኛውም ፎቶግራፎች ውሸት እና በተማሪዎች እና በኢራን የሚሠሩ በማኅበረሰብ አራማጆች ላይ የሚወጡ የተዛቡ የሞራል እሴት የሌላቸው ናቸው›› ብሏል፡፡ በጊዜው በመቶ የሚቆጠሩ ኢራናውያን ወንዶች ቀሚስ ለብሰው ራሳቸውን ፎቶግራፍ በማንሳት ታቫኮሊን በመደገፍ ከጎኑ ቆመዋል፡፡ | في ذلك الوقت ادعت السلطات بأن مجيد توكلي ارتدى زياً نسائيا ليتمكن من الهرب بعد إلقائه لخطاب في طهران في يوم الطالب، ولكن ناشطو حقوق الإنسان نشروا تقريراً من شاهد عيان يقول: “كل الصور التي يتم نشرها عن طريق إعلام الدولة مزيفة وهذا استخدام واضح لوسائل غير أخلاقية ضد الطلبة والناشطين المدنيين في إيران” في ذلك الوقت قام مئات من الرجال بتصوير أنفسهم وهم يرتدون زياً نسائياً وحجاباً لدعم مجيد توكلي. |