# | amh | eng |
---|
1 | ባህሬን፤ ዴሞክራሲና እስልምና አንድ ላይ መኖር ይችላሉ? | Bahrain: Can Democracy and Islam Co-Exist? |
2 | ‘በኢስላማዊ ማኀበረሰብ ዴሞክራሲ ሊኖር ይችላል? | Can democracy exist in Islamic societies? |
3 | 'ዛሬ ይህ ርዕስ በባህሬናውያን ጦማሪዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ | This was the topic of conversation between Bahraini bloggers today. |
4 | ጉዳየን ያነሳው የባህሬናውው አርቲስት አል ሻክህ ትዊት በማድረግ ነው [ar]: | Bahraini artist Al Shaikh raised the issue when he tweeted [ar]: |
5 | @Anas_Al_Shaikh፤ በኢስላማዊ ማኀበረሰብ ውስጥ ፓለቲካ ምን አንደሆነ እና ሀይማኖት ምን እንደሆነ ለመለየት አስቸጋሪ ነው፤ ለዚህም ይመስላል ምንም እንኳን ምርጥ ህገ መንግስት ብናዘጋጅም ሰላማዊ የስልጣን ሽክርክርን ብንቀበል ዴሞክራሲ ተሳክቶልን የማያውቀው፡፡ | @Anas_Al_Shaikh: It is difficult to separate between what is political and what is religious in Islamic societies and this is why democracy will never succeed even if we write the best constitutions and accept the peaceful rotation of power |
6 | ፊርለስ ባሪኒያ መለሰ፤ | Fearless Ba7rainia replies: |
7 | | @fearlessbahrain: Democracy is the solution and the remedy for such problems. |
8 | @fearlessbahrain፤ ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ዴሞክራሲ መፍትሔና ፈዋሽ ነው፤ ህጎች ከተዘጋጁ በተፈጥሮዓዊ መንገድ እየተሻሻሉ ይመጣሉ፡፡የሲቪል ማኀበረሰብ የኛ ህዝብ መድህን ነው፡፡ | If laws are developed, people will improve too in a natural way. A civil society is our people's savior |
9 | | Bahraini journalist Abbas Busafwan has another take. |
10 | ባህሬናዊው ጋዜጠኛ አባስ ቡሳፍዋን ሌላ መወሰድ አለው፤ ለአል ሻይክህ የመጀመሪያ ትዊት እንዲህ ሲል መለሰ፤ | He responds to Al Shaikh's original tweet saying: @abbasbusafwan: This conclusion is really painful. |
11 | @abbasbusafwan፤ ይህ ድምዳሜ በእውነት ያማል፤ ይህ በጅምላ መፈረጅ (generalization) ነው ፡፡ ምን አልባት ቱርክ የስኬት ተምሳሌት ልትሆን ትችላለች፡፡ | It could be a generalisation. Perhaps Turkey's example is a success |
12 | አል ሻይከህ መለሰለት፤ | Al Shaikh answers: |
13 | @Anas_Al_Shaikh፤ በቱርክ የሀይማኖት እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ሚዛናዊ አይደሉም፡፡ለምሳሌ በቱርክ የግብረ ሰዶማውያንን መብት አለ፤ እናም እኔ ራሴ በታዋቂው ታክሲም ጎዳና ተቃውሞ አይቻለው፡፡ | @Anas_Al_Shaikh: Turkey did not balance between religious and political issues. For instance, Turkey has rights for gays, and I saw them myself protesting on the famous Taksim street |
14 | አህመድ አል ሓዳድም ጨመረበት | And Ahmed Al-haddad adds: |
15 | @DiabloHaddad፤ ዛሬ ቱርክ በመራሔ አታቱርክ እንደነበረችው አይደለችም፤ ታዋቂው ኤርዶጋን ቱርክን ወደ ቅድመ አታቱክ ዘመን መልሷታል፡፡ | @DiabloHaddad: Turkey isn't today what it was during the rule of Ataturk. The famous Erdogan took Turkey to the pre-Ataturk era |
16 | ቡሳፍዋን በመልሱ ቀለደ፤ | In reply, Busafwan jokes: |
17 | @abbasbusafwan፤ ሳውዲ አረቢያ የዴሞክራሲ ምርጥ ምሳሌ ትመስለኛለች፤ ሹራ፣ ሰብዓዊ መብት፣ ነጻ ፕሬስ፣ በሀይማኖት እና ፓለቲካ መካከል ሚዛናውነት | @abbasbusafwan: I think that Saudi Arabia is the best example of democracy, Shura, Human rights, free Press, and balancing between religion and politics |
18 | አቡ ዮሲፍ በሃይማኖት እና ፖለቲካ አለመቀላቀል ይስማማል፤ | Abu Yousif agrees that politics and religion don't mix: |
19 | @xronos2፤ እስማማለው ሃይማኖት እና ፖለቲካን መቀላቀል የለብንም እነርሱ ግን አይስማሙም ከዚያም ልክ እንደኢራን ጨቋኝ ስርዓት ይኖረናል፡፡ | @xronos2: I agree. We shouldn't mix religion with politics for they don't agree and then we would become a repressive regime like Iran |
20 | አቡ ካሪም የምዕራባውያን የዴሞክራሲ ዘዬ ከውጭ ከምናመጣ ያለንን ማሻሻል ይገባናል ይላል፤ | And Abu Karim says we should improve what we already have instead of importing a Western-style democracy: |
21 | @AbuKarim1፤ ችግራችን ያለንን ከማሠስ እና እርሱን ከማዘመን ይልቅ በእኛ ማኀበረሰብ ላይ የምዕራባውያንን ንድፈ ዐሳብ ለመተግበር እንፈልጋለን፡፡ | @AbuKarim1: Our problem is that we want to implement Western theories on our societies instead of searching in what we have and modernising it |