# | amh | kor |
---|
1 | የትርጉም መርሐ ግብር፤ ዓለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነትን ጥበቃ መግለጫ | 번역 프로젝트: 글로벌 인터넷 자유 보호 성명서 |
2 | | 앞으로 일주일 동안 글로벌 보이스 각국 언어 봉사자들(Lingua volunteers) 공개 온라인 항의 성명서(public online petition)을 번역한다. |
3 | ለተከታዮቹ ሰባት ቀናት የዓለም ድምፆች የቋንቋ በጎ ፈቃደኞች፤ ህዝባዊ የመስመር ላይ የድጋፍ ፊርማን ይተረጉማሉ፡፡ ፊርማው በመጪው ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ህብረት (አይቲዩ) ጉባኤ ላይ የመስመር ላይ ሰብዓዊ መብት ጥበቃን የሚደግፍና የአይቲዩ አባላት የሆኑ መንግስታትን የበየነ መረብ ገሀድነት እንዲያከብሩ የሚጠይቅ ነው፡፡ | 해당 성명서는 온라인 인권 보호를 지지하고 국제전기통신연합(International Telecommunication Union, ITU)의 각국 대표단이 곧 개최될 ITU 컨퍼런스에서 각국 대표단이 인터넷 자유를 지지할 것을 촉구한다. |
4 | ለማንኛውም ግለሰብ ወይም የሲቪል ማኀበር ፊርማ ክፍት የሆነው አለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነት ጥበቃ መግለጫ እንዲህ ይነበባል፤ | 해당 성명서는 개인, 시민 단체 조직이 모두 서명할 수 있다. |
5 | በታህሳስ 3(እ. ኤ. | 글로벌 인터넷 자유 보호 성명서의 내용은 다음과 같다. |
6 | | 오는 12월 3일, 전세계 정부는 UN 산하기구인 ITU의 중요 조약을 업데이트하기 위해 모인다. |
7 | አ.) የዓለም መንግስታት ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ህብረት (አይ. ቲ. | 어떤 정부들은 ITU 권한을 확대해 인터넷 거버넌스에까지 영향을 미치길 원한다. |
8 | ዩ) የተሠኘውን የመንግስታቱ ህብረት ኤጀንሲ ቁልፍ ስምምነት ለማደስ ይገናኛሉ፡፡ አንዳንድ መንግስታት የበየነመረብ ገሐድነትና እና ፈጠራዎችን በሚገድብ፣ የመገልገያ ወጪን በሚጨምር፣ የመስመር ላይ ነጻነትን በሚሸረሽር መልኩ የአይቲዩ ስልጣን የበየነመረብ ገዢነት በመጨመር እንዲሰፋ ሐሳብ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡የሲቪል ማኀበራት ድርጅቶችና የሁሉም ሀገራት ዜጎች ዓለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነት ለመጠበቅ ይህንን መግለጫ እንዲፈርሙ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ | 그렇게 되면 인터넷 개방성과 혁신이 위협을 받고, 접근 비용이 증가되며, 온라인 인권이 훼손된다. 우리는 모든 국가의 시민 사회 조직과 시민들이 다음 글로벌 인터넷 자유 성명서에 서명하길 원한다. |
9 | የበየነ መረብ አስተዳደር ውሳኔዎች መደረግ ያለባቸው በግልጽነት በትክክለኛ ብዙኃን ባለድርሻ አካላት፣ በሲቪል ማኀበራት፣ መንግስታት እና የግሉ ማኀበረሰብ ተሳትፎ ነው፡፡ አይቲዩን እና አባል ሀገራቱን ግልጸኝነት እንዲመርጡና ምናልባት የመስመር ላይ ሰብዓዊ መብት እንቅስቃሴን የሚጎዳውን የአይቲዩ ስልጣን ወደ በየነ መረብ ገዢነት የመስፋፋት ምንም አይነት ሐሳብ ውድቅ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ | 인터넷 거버넌스 결정은 시민사회, 정부, 그리고 민간기업의 참여를 보장하는 다자간 협의체제를 통해서 이뤄져야 한다. 우리는 ITU와 회원국이 이러한 투명성을 수용하고 ITU의 권한을 인터넷 거버넌스에 확장하여 온라인 인권이 침해될 수 있는 우려를 불식시키길 바란다. |
10 | የተቃውሞውን ፊርማ ለማኖር ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ነጻነት ጥበቃን መካነ ድር ይጎብኙ፡፡ ለመፈረም የመጀመሪያ ስሞዎን፣ የቤተሰብ ስሞዎን፣ የበየነ መረብ አድራሻዎትን፣ የደርጅትዎን ስም (የሲቨል ማኀበራት ድርጅትን ወክለው የሚፈርሙ ከሆነ)፣ የደርጅትዎን መካነ ድር ያስገቡ፤ ሀገርዎን ከዝርዝሩ ውስጥ ይምረጡ፡፡ | 성명서에 서명하기 위해서는 글로벌 인터넷 자유 웹사이트(Protect Global Internet Freedom website)을 이용한다. 서명을 위해서는 본인 이름, 이메일 주소, 단체 이름 (시민단체 대표로서 서명하는 경우), 단체 URL, 그리고 자신의 국가를 택하면 된다. |
11 | ሁሉም ትርጉሞች በተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰቢያው መካነ ድር መቀመጫውን ካናዳ ባደረገው የዲጂታል መብቶች ቡድን ኦፕንሚዲያ ወደመስመር ላይ በሚሰቅለው ላይ ይለጠፋሉ፡፡ | 모든 번역문은 성명서 웹사이트에 게시된다. 웹사이트는 캐나다의 디지털 권리 단체인 오픈미디어(OpenMedia)가 게시되어 있다. |
12 | እባክዎን ትርጉሙ በሚታይበት ጊዜ(ከላይ ያለውን ይመልከቱ) በማኀበራዊ ሚዲያዎች ለወዳጆቻችኹ ለማጋራት የበረታችኹ ሁኑ፡፡ | 위에서 보는 것처럼 번역문이 올라올 때마다 이 링크들을 SNS와 다른 친구들에게 공유하자! |