# | amh | spa |
---|
1 | የኢትዮጵያ ዞን ፱ ጦማሪያን የአለምአቀፍ ህግ ድክመቶች ተጋርጦባቸዋል | Los blogueros etíopes de Zone9 se enfrentan a los límites del derecho internacional |
2 | የዞን ፱ አባላት አብረው አዲስ አበባ ውስጥ ሳሉ፣ እ. ኤ. | Miembros de Zone9 reunidos en Adís Abeba, en 2012. |
3 | አ. 2012 ዓ. | Foto utilizada con permiso. |
4 | ም. ። ፎቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ፍቃድ ተሰጥቷል። | Este artículo se publica conjuntamente con el blog de World Policy Journal. |
5 | ይህ ልጥፍ ከWorld Policy Journal ጦማር ጋር በመተባበር የታተመ ነው። | El sistema internacional de derechos humanos no funciona ─ o quizás nunca funcionó en absoluto. |
6 | የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ስርዓት የተሰናከለ ነው - እንዲያውም መጀመሪያውኑ ሰርቶ ላያውቅ ይችላል። በብዙ ጉዳዮች ላይ እንደታየው ከሆነ የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች በየአገራቸው ብሔራዊ ህጎች ይጣሳሉ፣ ምንም እንኳ በተባበሩት መንግስታት ሁለገብ አዋጅ (United Nations' Universal Declaration)፣ እና በአውሮፓ የደህንነት እና የትብብር ድርጅት፣ በየአሜሪካ አገራት ድርጅት፣ በአፍሪካ ኮሚሽን እና በሌሎች ውስጥ ያሉ ቃል የተገባባቸው የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ቢያካትቱም። | Caso tras caso, se violan los derechos humanos de los ciudadanos con arreglo a las leyes nacionales de sus respectivos países, a pesar de la existencia de compromisos internacionales de derechos humanos en la Declaración Universal de las Naciones Unidas, y la Organización para la Seguridad y la Cooperación en Europa, la Organización de Estados Americanos y la Comisión Africana, entre otros. |
7 | የአለምአቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤቱ አይን ካወጡት በስተቀር ማንኛውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ማድረግ የሚችለው ነገር የለም፣ እና አባል አገራት ፍትህ በመሠላቸው መልኩ የመስጠት ሰፊ ነጻነት አላቸው። | El Tribunal Penal Internacional tiene escasa influencia salvo en casos de las más atroces violaciones de derechos humanos internacionales, y los Estados miembros tienen un amplio margen para impartir justicia como mejor les parece. |
8 | ሐሳብን የመግለጽ መብትን የሚጠብቁ የገዛ ህጎቻቸውን ማክበር ወይም ማስፈጸም ባልቻሉ አገሮች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች አለምአቀፍ መርሖዎች እውነተኛ መፍትሔ ቢሰጣቸውም ከስንት አንዴ ነው። | Para quienes viven en países que no ofrecen o aplican sus propias leyes destinadas a proteger la libertad de expresión, los principios internacionales rara vez han proporcionado vías de recurso. |
9 | ዛሬ ዞን ፱ ተብሎ በሚታወቀው ነጻ የኢትዮጵያውያን ጦማሪያን ቡድን ላይ እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። | Actualmente, este es el caso del colectivo independiente de blogueros etíopes conocido como Zone9. |
10 | ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ስድስት የዞን ፱ አባላትን ሶስት ቅርበት ካላቸው ጋዜጠኞች ጋር በአዲስ አበባ ውስጥ አስሯል። | En abril de este año, el gobierno de Etiopía arrestó a seis miembros de Zone9 junto con tres colegas periodistas en Adís Abeba. |
11 | ምንም ክስ ሳይመሰረትባቸው ለወራት የተያዙ ሲሆኑ ከሌሎች ጋር እንዳይገናኙም ተከልክለዋል። | Fueron retenidos durante meses sin cargos formales y se les negó la posibilidad de comunicarse. |
12 | ሐምሌ ላይ ከእስር ቤት የወጣው የበፍቃዱ ኃይሉ ማስታወሻ እና እንዲሁም በፍርድ ቤት ውስጥ የተሰጡ ቃሎች በደል እና ተደጋጋሚ ድብደባዎች እንደደረሰባቸው ያስረዳሉ። | El testimonio de Befeqadu Hailu, uno de los blogueros acusados, sacado clandestinamente de la cárcel en agosto, así como las declaraciones ante el tribunal, alegan malos tratos y frecuentes palizas. |
13 | እነዚህ ዘጠኝ ሰዎች «የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሆኑ ከሚያስመስሉ የውጪ ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት…በማህበራዊ ገጾች በኩል የሕዝብ አመጽ ለማነሳሳት ገንዘብ ተቀብለዋል» በሚሉ ውንጀላዎች ተይዘዋል። | Extraoficialmente, los nueve permanecen detenidos por acusaciones de “trabajar con organizaciones extranjeras que dicen ser defensoras de los derechos humanos y…recibir financiación para incitar a la violencia pública a través de los medios sociales”. |
14 | ሐምሌ ላይ የዞን ፱ እስረኞች መንግስት በይፋ አሸባሪዎች ብሎ ከሰየማቸው የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች ድጋፍ በመቀበል እና በአለምአቀፍ ተሟጋቾች ታክቲካል ቴክኖሎጂ ኮሌክቲቭ (Tactical Technology Collective) ከተባለው ጋዜጠኞች እና ተሟጋቾች እራሳቸውን ከዲጂታል ክትትል እንዲጠብቁ ከሚያግዛቸው ቡድን በኢሜይል ኢንክሪፕሽን እና ዳታ ሴኩሪቲ ስልጠና በመቀበል በ2001 ኢትዮጵያ ጸረ-ሽብር አዋጅ ተከስሰዋል። | En julio, los prisioneros de Zone9 fueron acusados en virtud de la Proclamación contra el Terrorismo de 2009 etíope de recibir apoyo de organizaciones políticas de la oposición declaradas formalmente por el gobierno como terroristas, y de recibir formación de activistas internacionales en cifrado de correo electrónico y seguridad de datos del Tactical Technology Collective, un grupo que ayuda a periodistas y activistas a protegerse de la vigilancia digital. |
15 | የዞን ፱ ጦማሪያን በቅርብ ጊዜ በነበረው የአረብ አመጾች ላይ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰቱ በሚችሉ ተመሳሳይ አመጾች የዘገበው እስክንድር ነጋን ጨምሮ በተመሳሳይ ህጎች ከተነጣጠሩ ሌሎች የሚዲያ ድምጾች ጋር ተቀላቅለዋል። | Los blogueros de Zone9 se suman a otros medios de comunicación que también fueron blanco de leyes similares, entre ellos Eskinder Nega, que había informado sobre los recientes levantamientos árabes y la posibilidad de que se produjeran levantamientos similares en Etiopía. |
16 | በቁጥጥር ስር ውሎ በ«ሽብርን በማቀድ፣ ዝግጅት በማድረግ፣ በማሴር፣ በማሳመጽ እና ሙከራ በማድረግ» ተከስሶ የ18 ዓመት እስር ተፈርዶበታል። | Fue arrestado y acusado de “planificar, preparar, conspirar, instigar e intentar” cometer actos terroristas, y condenado a dieciocho años de prisión. |
17 | የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያደረጓቸው አለምአቀፍ ስሞታዎች በጉዳዩ ላይ ተጽዕኖ አልነበረውም። | Los llamamientos internacionales de organizaciones de defensa de derechos humanos han tenido escaso efecto sobre el caso. |
18 | ግንቦት ላይ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒሌይ እንዲህ ብላ የሚያብራራ ቃል ሰጥታለች፣ | En mayo, la Alta Comisionada de las Naciones Unidas para los Derechos Humanos, Navi Pillay, publicó un comunicado explicando, |
19 | በሽብርተኝነት ላይ የሚደረገው ዘመቻ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አባላትን ለማስፈራራት እና ድምጽ ለማጥፋት እንደ ሰበብ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም። | La lucha contra el terrorismo no puede servir de excusa para intimidar y silenciar a los periodistas, blogueros, activistas de derechos humanos y miembros de organizaciones de la sociedad civil. |
20 | እና ደግሞ ከውጪ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት እንደ ወንጀል ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም። | Y trabajar con organizaciones extranjeras de derechos humanos no puede ser considerado un delito. |
21 | በተጨማሪም፣ ሰባት የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች እና የፕሬስ ነጻነት ድርጅቶች በላኩት አስቸኳይ ጥያቄ የአፍሪካ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት በዞን ፱ ላይ በተከፈተባቸው ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል። | Además, siete organizaciones internacionales de derechos humanos y libertad de prensa urgieron a la Comisión Africana y las Naciones Unidas en un llamamiento urgente a intervenir en el caso contra Zone9. |
22 | ጥያቄው ጉድለት ባለው የክሶቹ ግልጽነት እና ተከሳሾቹ በቂ የህግ ምክር የማግኘት መብት ላይ ያተኮረ ነው። | El llamamiento se centraba en la ausencia de cargos precisos y la negativa a permitir que los acusados tuvieran representación legal adecuada. |
23 | የሚዲያ ህግ መከላከያ ተነሳሽነት (Media Legal Defence Initiative) ጠበቃ እና የጥያቄው መሪ ፈራሚ የሆነችው ናኒ ጃንሰን በኢሜይል ውስጥ ሁለቱም የአፍሪካ ኮሚሽን እና ተመድ «በእነዚህ ጉዳዮች ቀዳሚ ደረጃዎች ላይ በሚስጥራዊነት ስም ነው የሚሰሩት» ብላ ጽፋለች። | Nani Jansen, abogada de Iniciativa de defensa legal de medios y firmante principal del llamamiento, escribe en un correo electrónico que la Comisión Africana y la ONU “operan bajo el manto de la confidencialidad en las fases iniciales de estos asuntos”. |
24 | እንዲህ ብላ ትቀጥላለች፦ | Y continúa: |
25 | ከአንድ መንግስት ጋር አንድ ጉዳይ ሲከታተሉ የውጪውን ዓለም ሳያሳውቁ ነው። | Cuando hacen un seguimiento con un gobierno, esto se hace sin informar al mundo exterior. |
26 | ብዙ ወራት (አብዛኛው ጊዜ ከዓመት በላይ) ካለፉ በኋላ ብቻ ነው ከአንድ መንግስት ጋር የተደረጉት እነዚህ ልውውጦች ለበላይ አካሉ በሚደረገው የእንቅስቃሴ ስልት ሪፖርት ላይ የሚታተመው። | Estos intercambios con un gobierno solo se publican en el informe del mecanismo ante su organismo supervisor muchos meses (a menudo más de un año) después, |
27 | ስለዚህም፣ ማንኛውም ጣልቃ መግባት ዞን ፱ በሚወክለው የድምጽ ማፈኛ ስርዓት ውስጥ ይገባል-ከሕዝባዊ እይታ ወይም ተሳትፎ ተደብቆ። | Por tanto, cualquier intervención se suma al resto del cono de silencio que es Zone9 - sin estar sometida a ningún tipo de escrutinio o participación pública. |
28 | እነዚያ አካላት ጉዳዩን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቢከታተሉትም እንኳ ያላቸው አማራጭ የተገደበ ነው። | Aunque estos organismos hagan una labor de seguimiento con el gobierno etíope, sus vías de recurso son limitadas. |
29 | በአስቸኳይ ጥያቄው ላይ በጻፈችው ጽሑፍ ጃንሰን የአፍሪካ ኮሚሽን እስራቶቹን በአቋም ማውገዝ እንደሚችሉ፣ የሁለቱም ድርጅቶች ሪፖርት ጸሐፊዎች ምርመራ ለማካሄድ ወደ ኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ጉብኝቶችን እንዲያደርጉ መጠየቅ እንደሚችሉ፣ እና ኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል እንደመሆኗ መጠን እንደዚህ ያለ ጥያቄ የማክበር ግዴታ እንዳለባት አውስታለች። | En un artículo sobre la petición urgente, Jansen señala que la Comisión Africana puede condenar las detenciones en una resolución, que los relatores de ambas organizaciones pueden solicitar visitas oficiales a Etiopía para investigar, y que Etiopía, como miembro del Consejo de Derechos Humanos de la ONU, estaría obligada a honrar esa petición. |
30 | ነገር ግን እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎች ቢቀርቡ እና መርመራዎች ቢካሄዱም እንኳ ሊገኙ ይችላሉ ተብሎ የሚገመቱት ውጤቶች በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የማስፈጸም ዕድሉ በጣም አነስተኛ ነው። | Pero incluso si se realizaran tales solicitudes y se llevaran a cabo las investigaciones, hay pocas posibilidades de obligar al gobierno etíope a cumplir las hipotéticas conclusiones. |
31 | ጥያቄው ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት በተከሳሾቹ ላይ በክሱ እንደቀጠለበት ነው። | Desde que se hizo ese llamamiento, el gobierno etíope ha procedido con los cargos contra los acusados. |
32 | በችሎቱ ላይ ያሉ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ለተከሳሾቹ ቅርብ በሆኑ ወዳጆች በሚሄድ የችሎት መከታተያ ጦማር (Trial Tracker Blog) ላይ ማግኘት ይቻላል። | Puede encontrar los últimos detalles sobre el juicio en el blog de seguimiento del juicio, un sitio gestionado por gente cercana a los acusados. |
33 | እንደ የ#Freezone9bloggers የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚፈጽማቸው ጥሰቶችን ይፋ ለማውጣት የሚደረጉ ይፋዊ ጥረቶች ቀጥተኛ ያልሆነ ውጤት ነው ያላቸው። | Los intentos públicos por destacar las transgresiones del gobierno etíope contra los derechos humanos, como la campaña en los medios sociales bajo la etiqueta #Freezone9bloggers, tienen un efecto indirecto. |
34 | ለእስረኛዎቹ የተሻለ አያያዝ እንዲኖር ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ መንግስትን ለማሳፈር ያለሙ ናቸው። | Intentan avergonzar al gobierno etíope para garantizar un mejor trato para los presos. |
35 | እንዲሁም በአለምአቀፍ ድርጅቶች እና እንደ ለኢትዮጵያ መንግስት ወሳኝ የጦር እና የደህንነት አጋር በሆነችው አሜሪካ ያሉ ተባባሪዎች ላይ ጫና ለማሳረፍም ያለሙ ናቸው። | También buscan presionar a organismos internacionales y aliados de Etiopía, como Estados Unidos, para quien Etiopía es un socio militar y de seguridad fundamental. |
36 | ተስፋ የሚደረገው እነዚያ ድርጅቶች በተራቸው ኢትዮጵያ የዞን ፱ ተከሳሾችን ነጻ እንድታወጣ የፖለቲካ ጫና እንዲያሳርፉ ነው። | La esperanza es que esas organizaciones a su vez ejerzan presión política sobre Etiopía para liberar a los acusados de Zone9. |
37 | እንግዲህ በአለምአቀፍ ደረጃ ቃል የተገባባቸውን ነገሮች መተግበር የሚወሰነው እየሰራ እና ተፈጻሚነት ባለው የህግ ስርዓት ሳይሆን በዋነኝነት በድርድር የሚካሄድ የፖለቲካ ሂደት ነው የሚመስለው። | La aplicación de los compromisos internacionales parece depender principalmente de un proceso político negociado, no de un sistema legal funcional y aplicable. |
38 | ኢትዮጵያ ውስጥ ለፖለቲካዊ ዓላማ ሲባል ህጉ ምን ያህል በቀላሉ ስራ ላይ እንደሚውል ወይም ችላ እንደሚባል ሲታይ ጉዳዩ ለእነሱ እንዲፈታላቸው ያለው ተስፋ ፖለቲካዊ ጫና ብቻ መሆኑ ሲታይ ነገርየው ከባድ ምጸት ነው። | Teniendo en cuenta la facilidad con que se aplica o se ignora la legislación nacional en Etiopía con fines políticos, es una triste ironía que solo la presión política pueda aspirar a resolver el caso a su favor. |