# | amh | swe |
---|
1 | በጃፓን ሦስት ጎንዮሽ (3D) የቡና ጥበብ | Japansk kaffekonst i 3D |
2 | ከትኩስ መጠጦች ሁሉ አረንጓዴ ሻይ የመጀመሪያ ተመራጭ መጠጥ በሆነባት ምድር፣ በወተት አረፋ በስሪ ዲ ጥበብ የሚሠራ የቡና ጥበብ ብዙዎችን ልብ ማርኳል፡፡ | I landet där grönt te fortfarande är den populäraste varma drycken, vinner tredimensionell kaffekonst nya beundrare [en] för varje skummande kopp. |
3 | | Allt fler kafébesökare i Japan, inspirerade av populära bilder inom sociala medier som visar hur ångande mjölk reser sig upp ur kaffekoppar som små konstverk, ber att deras latte dekoreras med något lite extra. |
4 | በጃፓን ካፍቴሪያ ጎብኚዎች በማኅበራዊ ድረገጽ በሚታዩ የማኪያቶ ፎቶግራፎች በመማለል የሚጠጡት ማኪያቶ በምስሎች አሸብርቆ በተለያዩ ምስሎች ታጅቦ እንዲቀርብላቸው ይጠይቃሉ፡፡ | Kaffet är ingen främmande dryck i Japan. |
5 | | Den japanska kaffeindustrins egna organisation All Japan Coffee Association [en] har rapporterat [en] att Japan ligger på tredje plats ibland importländerna vad gäller sammanlagd konsumtion. |
6 | ጃፓን ለቡና እንግዳ አገር አይደለችም፡፡ መላው የጃፓን ቡና ማኅበር እንዳቀረበው ሪፖርት ጃፓን በዓለም ቡና ወደ አገራቸው ከሚያስገቡ አገሮች በተጠቃሚነት የሦስተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ | År 2010 vann japanen Haruna Murayama [en] världsmästerskapen i “latte art”, World Latte Art Championship [en]. |
7 | በ2010 የጃፓኑ ሃሩና ሙራያማ ዓለም አቀፍ የማኪያቶ ጥበብ ሻምፒዮና አሸናፊ ሆኗል፡፡ | Platt kaffekonst är redan populär över hela önationen. |
8 | በውኃ በተከበችው ይህች አገር የተለያዩ ጠፍጣፋ የማኪያቶ ቅርፆች የተለመደ ነው፡፡ በቲውተር በተደረገ የማኪያቶ ጥበብን[ja] ፍለጋ ግን በርካታ ፎቶዎች የተገኙ ሲሆን የተለየ ጥበብ ያላችው በልብ ቅርፅ፣ በቅጠል ቅርፅ፣ ድብ ቅርፅ (ቴዲ ቤር)፣ ታዋቂ የካርቱን ፊልም ተዋኒያን እንዲሁም የኢንተርኔት ምልክቶች ሳይቀሩ ተገኝተዋል፡፡ | Ett sök efter “latte art” [ja] på Twitter resulterar i en mängd bilder av vackra kaffedrycker dekorerade med hjärtan, blad, nallar, populära animefigurer och till och med webbloggor [en]. |
9 | በቶኪዮ ዓለም አቀፍ ሄንዳ ኤርፖርት ውስጥ የሚገኝ የቡና መሸጫ በታዋቂው ዮጂያ ኮስሞቲክስ ኩባንያ ዲዛይን የተደረገ የጃፓን ሴት ምስል ያለበት ካፑችኖም ሳይቀር አቅርቧል[ja]፡፡ የዩ ቲዩብ ተጠቃሚው ኖዋቱ ሱጊ እንዴት አድርጎ በቡና እና በቸኮሌት አማካኝነት ማኪያ ላይ ምስሎችን መስራት እንደቻለ ያብራራል፡፡ | En kaffeautomat på Haneda Airport, Tokyos internationella flygplats, serverar till och med cappuccino [ja] med bilden av ett klassiskt japanskt kvinnoansikte, designad och producerad av Kyotos välkända kosmetikföretag Yojiya [en]. |
10 | | YouTube-användaren Nowtoo Sugi laddade upp följande video som visar hur han använder kaffesirap för att måla en tecknad-serie-karaktär i en kopp latte: |
11 | አዲስ ደረጃ መድረስ | Når nya höjder |
12 | ነገር ግን አንዳንድ ባሬስታዎች የዚህ የቡና ላይ ምስል የመፍጠር ችሎታ ክስተት በወተት አረፋ አማካኝነት በሶስት ጎን (ስሪ ዲ) እይታና ቅራፅ ወደ አዲስ ደረጃ አድርሰውታል፡፡ | Men baristas har tagit detta kreativa kaffefenomen till nya höjder med skummande 3D-skulpturer. |
13 | ስሪ ዲ ማኪያቶ ጥበብ በቲውተር ተጠቃሚ @george_10g “ድመቷ ወርቃማ ዓሣዎችን ስትመለከት” | Latte-konst i 3D av Twitteranvändaren @george_10g: “En katt tittar på guldfisk.” |
14 | | Kazuki Yamamoto (@george_10g), “latte art”-mästaren som laddar upp sin kaffekonst på Twitter, skrev i sin blogg att han jobbar på ett belgiskt ölhus i Osaka. |
15 | ካዙኪ ያማሞቶ (@george_10g) በማኪያቶ ላይ ምሰል በመስራት ጥበብ ሊቅ፣ ይህንን ምስል በቲውተር ገፁ ያስቀመጠ ሲሆን በራሱ ጦማር ላይ በኦሳካ ቤላጊአን ቢራ ቤት እንደሚሰራ ፅፏል፡፡ የማኪያቶ ጥበቦቹን “የትርፍ ጊዜ ካፕችኑ” እያለ ይጠራቸዋል፡፡ በድብርት አሊያም በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ ቢሆኑም ግን ትልቅ ችሎታ እና የስራ ፍቅር የሚጠይቁ ናቸው ይላል፡፡ በአንድ ወቅት ከዚህ በፊት ማኪያቶ ላይ የሰራቸውን ምስሎች ሰብስቦ በቲውተር ገፁ ላይ ለጥፏቸው ነበር፡ | Han kallar sin kaffekonst “fritids-cappuccino” [暇カプチーノ], en skapelse som kommer ur tristess eller lediga stunder, naturligtvis skapade med stor ansträngning och kärlek. I ett inlägg på Twitter erinrade han sig vid ett tillfälle den oändliga mängd konstverk han skapat i kaffe: |
16 | | @george_10g: Jag började måla på kaffe år 2011 och år 2012 hade jag målat och serverat ungefär 1000 koppar, men på något vis minns jag fortfarande när och vad jag målat och vem jag serverade det. Det är lite läskigt. |
17 | | Twitter-användare @petakopetako svarade [ja] på kommentaren med att berömma hans talang: |
18 | @george_10g:በማኪያቶ ላይ ምስል መስራት የጀመርኩት በ2011 ነው፡፡ በደፈናው እስከ 2012 ድረስ በማኪያቶ ላይ ምስል ሰርቼ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን አስተናግጃለሁ፡፡ ነገርግን በሚገርም ሁኔታ መቼ እና ምን እንዲሁም ለማን የምስል ማኪያቶዎቹን እንደሰራሀትና እንዳስተናገድኩ አስታውሳለሁ፡፡ ነገሩ ትንሽ የማይገባ ነገር ነው፡፡ | @petakopetako: Jag tycker om att ta bilder. Vanligtvis är jag dålig på att komma ihåg människors ansikten, men när jag tagit bilder av dem minns jag platsen och vad de pratade om. |
19 | የቲውተር ተጠቃሚ @petakopetako አድናቆቱን በመስጠት እና ሥራዎቹ ልዩ መሆናቸውን በመናገር ምላሽ[ja] ሰጥቶታል፡ | Kanske människor kommer ihåg saker bättre när de gör någonting de känner passionerat för. |
20 | @petakopetako ፡ ፎቶ ማንሳት እወዳለሁ፡፡ በመደበኛ ሁኔታ የሰዎችን ፊት አይቼ የት እንደማውቃቸው ማስታወስ አልችልም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ፎቶ ካነሳኃቸው፣ ፎቶውን የት እንዳነሳኃቸው፣ ፎቶውን ሲነሱ ምን እያወሩ እንደነበር ማስታወስ እችላላሁ፡፡ ምናልባት ሰዎች የማስታወስ ችሎታቸው የተሻለ የሚሆነው የሚወዱትን ስራ በሚሰሩበት ወቅት ይሆናል፡፡ | Kaféägare och baristas i Japan har laddat upp bilder av den hemliga, tredimensionella kaffekonsten - inte nämnd på någon meny - på sociala medier. Dessa bilder cirkulerades vitt och brett och drog till sig uppmärksamhet från lokala TV- och radiostationer samt tidningar. |
21 | የማኅበራዊ ድረ ገፆች ተፅእኖ በጃፓን የሚገኙ የካፍቴሪያ ባለቤቶችና ባሬስታዎች ባለሦስት ጎን ምስል(ስሪ ዲ) እይታ ያላቸውን የማኪያቶ ፎቶግራፎች ሜኑ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ላይ ጫኑ፡፡ እነዚህ ምስሎች በከፍተኛ ሁኔታ ሲሰራጩ አፋታም ሳይቆይ የአገሪቱን መፅሔቶች፣ ሬዲዮኖችና ቴሌቭዥኖች ቀልብ ለመግዛት ችለዋል፡፡ | Publiciteten har gett en del kaféer så många nya kunder att ägarna har svårt att hinna med. Ägaren till Cafe Bar Jihan i Shizuoka-länet skrev om Facebook-effekten i sin blogg [ja]: |
22 | በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች እና ማህበራዊ ገፆች የስሪ ዲ ማኪያቶ መሰራጨት ደንበኛ ለማግኘት ለሚሯሯጡ የቡና መሸጫ ቤት ባለቤቶች የተለያ አዳዲስ ተጠቃሚዎች እንዲመጡ መንገድ ከፍቶላቸዋል፡፡ በሺዞካ ክልል የካፌ ባር ጂሃን ባለቤት በጦማሩ ላይ ስለ ፌስቡክ ተፅእኖ ሲፅፍ [ja]: | Jag började servera tredimensionell kaffekonst på begäran av en av mina stamgäster. Jag laddade upp bilden på en Facebook-sida för skojs skull, och blev förvånad över det stora antal människor som gillade bilden. |
23 | ባለሦስት ጎን ምስል (ስሪ ዲ) ማኪያቶ መስራትና መሸጥ የጀመርኩት የረጅም ጊዜ ደንበኛዬ እንድሰራለት ከጠየቀኝ በኃላ ነው፡፡ ከዚያም ፎቶ ግራፍ አንስቼ በፌስቡክ ገፄ እንደው እንደ ቀልድ አስቀመጥኩት፣ በኃላ ፎቶዎቹንየወደዱ በርካታ ሰዎች ቁጥር ሳይ በጣም ነው የተደነቅኩት፡፡ ምስሎቹን ሰዎች በራሳቸው መንገድ ሲቀባበሏቸው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የኔን ቡና ቤት በተመለከተ የዜና ሽፋን መስጠት እንደሚፈልጉ ጠየቁኝ ፡፡ በቶኪዮ ቴሌቭዥን እንድቀርብ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ግራ ገብቶኝ ነበር፡፡ | Som en följd av vår förhöjda profil bad flera medier mig om att få göra reportage om vårt kafé. Jag blev lite förvirrad när jag ombads uppträda på TV i Tokyo! |
24 | Facebook photo by caffe.bar.jihan. | Facebook-bild av caffe.bar.jihan. |
25 | A cat is taking a bath in espresso coffee. | En katt badar i espresso. |
26 | እንዲህም ጽፏል [ja]: | Han skrev även [ja]: |
27 | | Min katt-kaffekonst tar så lång tid att skapa att jag inte kan ta emot beställningar på den när vi har fullt upp i kaféet. |
28 | በጥቁር ቡና ገንዳ ውስጥ የተዘፈዘፈችውን ድመት ማኪያቶ ለመስራት ብዙ ሰዓት ይወስዳል፡፡ በካፍቴሪያችን ውስጥ ብዙ ተስተናጋጅ ደንበኞች እያሉ ይህንን ለመስራት ትዕዛዝ መውስድ አልችልም፡፡ ይህንን ነገር ምን ላድርገው ብዬ ከራሴ ጋር ብዙ ተሟግቻለሁ፡፡ ቢያንስ ካፌያችን ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ በስራ ቀናት ቀዝቀዝ ይላል ስለዚህ እርሶ ካፍቴሪያችንን የሚጎበኙት ለስሪ ዲ ማኪያቶ ብለው ከሆነ በዚህ ሰዓት ቢመጡ ይመረጣል፡፡ | Jag har grunnat över hur jag ska lösa situationen. Det är åtminstone lite lugnare på kaféet efter kl 18 under veckan, så om ditt besök gäller tredimensionell kaffekonst ber jag dig komma då. |
29 | ይህ ጽሑፍ በመጀመሪያ የተፃፈው በአያኮ ዮኮታ ነው፡፡ ኬኢኮ ታናካ አርዕቶ ሰርታለች፡፡ ኤል ፊኒች በድጋሚ አርዕቶ አድረጋለች፡፡ | Detta inlägg skrevs ursprungligen av Ayako Yokota. |
30 | @petakopetako ፡ ፎቶ ማንሳት እወዳለሁ፡፡ በመደበኛ ሁኔታ የሰዎችን ፊት አይቼ የት እንደማውቃቸው ማስታወስ አልችልም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ፎቶ ካነሳኃቸው፣ ፎቶውን የት እንዳነሳኃቸው፣ ፎቶውን ሲነሱ ምን እያወሩ እንደነበር ማስታወስ እችላላሁ፡፡ ምናልባት ሰዎች የማስታወስ ችሎታቸው የተሻለ የሚሆነው የሚወዱትን ስራ በሚሰሩበት ወቅት ይሆናል፡፡ | Keiko Tanaka redigerade hennes inlägg assisterad av L. Finch. |