# | amh | zht |
---|
1 | ስለፍቅርና የፍቅር ጨዋታ ከአንጎላ | 源自安哥拉--性與愛的傳說 蘿西. |
2 | ወጣቷ ሮዚ አልቬስ አንጎላዊ ጦማሪ (cronista) ናት፡፡ መኖሪያዋን ያደረገችው በአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ውስጥ ነው፡፡ “cronista” ማለት በፖርቱጋል ቋንቋ መጦመር የሚለውን ቃል ተስተካካይ ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን - ፅሁፎቹ ባብዛኛ ጊዜ በጋዜጣ የሚታተሙ ታሪኮች አንዳንዴ እውነተኛ ተሪኮች ሌላ ጊዜ ደግሞ የፈጠራ ልብ ወለዶች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ የራስ ችሎታን በአጭሩ ያሳያሉ፡፡ | 艾爾維斯是住在安哥拉首都羅安達的年輕部落客與「crónica」作家。「crónica」是一種源自葡萄牙的寫作風格,非常適合部落格寫作。 這類傳說故事原先刊登在報紙上,傳說有時是真,有時是假,但都包含某種意義或奇想,並會以簡短的方式呈現。 |
3 | “Sweet Cliché” በተሰኘው ጦማሯ አልቬስ አጫጫር ታሪኮችን የምትፅፍ ሲሆን፣ በአብዛኛው ስለፍቅር እና ስለፍቅር ጥብቅ ግንኙነቶች ትፅፋለች ( Bolgspot የፅሑፎቿ እንባቢዎች እድሜቸው ለፅሑፉ የሚመጥን ስለመሆኑ ያስጠነቅቃል)፡፡ከዚህ በታች ሰሞኑን በጣም አነጋጋሪ የነበረው ፅሑፏ ቀርቧል፡፡ “I killed my love” (“ፍቅሬን ገደልኩት”):- | 在蘿西的部落格「甜蜜的陳腔濫調」裡,她常常寫簡短的文章,通常是有關情愛或親密的相遇(部落格官方網站提醒讀者其部落格裡有成人內容)。 以下是從她最新也最受歡迎的文章「吾殺吾愛」節錄下來的一段文字: |
4 | | 在一個濕冷的夜裡,我站在家門前。 |
5 | በዚያ ቀዝቃዛና ዝናባማ ምሽት፣ ወደ ቤቱ መግቢያ በር ላይ፡፡ እንዴ ብቻ ልቡ ላይ፣ በጭካኔ እና ርህራሄ በጎደለው መንፈስ ፣ ለደስታዬና ለጉዳቴ ስል ፍቅሬን ገደልኩት፡፡ ፍቅሬ ሲሞት ተሰማኝ- ደም፣ ቀዩ እብጠት እቀነሰ ሲገረጣ ደሙ እየተንዠቀዠ ፈሰሰ… | 無情又殘忍的,我往心上搥了一記,我殺了我的愛,那讓我又愉悅又痛苦的愛。 我感覺愛在死去,那紅色的團塊,隨著血的流失,慢慢失去了色彩。 |
6 | ቀዝቃዛ ነበር፣ ፍቅሬ ቀስ እያለ ወደ መሬት ሲወድቅ የደም ባህር ሰራ፡፡ ሁለም ነገር ጭው ያለ መሰለ፣ አብረን ያሳለፍናቸው እነዛ መልካም ቀናቶችን አሰብኳቸው ፣ፍቅሬ ያደለኝን የደስታ ቀናቶች፣ ግን ደግሞ ወዲያው የፍቅሬ ክህደት ጭንቅላቴን ተቆጣጠረው፡፡ | 我看著我的愛,冷冷的,又小心翼翼的慢慢跌落,於是血海成形了。 所有的事物圍著我旋轉。 |
7 | ዝናብ ለመከላከል ጭንቅላቷ ላይ ፌስታል አድርጋ ጠደፍ ጠደፍ እያለች የምትራመደው ሴት ባየችው ነገር አንዳችም የተረበሽች አትመስልም፡፡ | 我憶起我們一起擁有的美好時光,以及我的愛帶給我的歡樂。 但腦海裡的影像立即又回到我的愛背叛我的那天。 |
8 | ቁጥራቸው እያደገ በመጣው ወጣት አንጎላውያን ጦማሪዎች ዘንድ የ21 አመቷ አልቬስ ልዩ ስፍራ እንደያዘች ትናገራለች፣ ምንም እንኳን እውቅናዋ ከአገሯ ይልቅ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ቢሆንም፡፡ግንኝነቱ ውስን እና አስተማማኝ ባልሆነው 3ጂ ኢንተርኔት ግንኙነት አማካኝነት በቅርቡ አልቬስን ቃለመጠይቅ አድርገንላት ነበር- ይበልጥ ለማወቅ | 一個拿著塑膠袋遮雨的女人跑了過去,但她彷彿並不在意自己看到的一切。 僅僅只有二十一歲,艾爾維斯就已經在愈來愈壯大的安哥拉部落格圈裡,佔據了一個獨特的位置,儘管她在國外的名聲是大過於國內。 |
9 | ሮዚ ላለፉት ሶስት አመታት ስትጦምር በቆየችባቸው ጌዜያቶች የቲውተር መለያዋ (@rosie_alves), “አትከተሉኝ፣ጠፍቻለሁ” | 我們最近透過非常不穩的3G連線,邀請她受訪,以下就是訪問的內容。 蘿西已經在部落格上寫作三年了。 |
10 | | 雖然蘿西在推特的自我介紹(@rosie_alves)裡寫道「不要追隨我,我是迷路的」,但她在網路上還是有一群為數眾多的粉絲。 |
11 | GV: የምትፅፊበትን የአፃፃፍ ስልት እንዴት ትገልጪዋለሽ? | GV:你會怎麼形容你所寫的文章類型? 我喜歡寫故事類型的crónica,有時我只會用對話的方式來寫。 |
12 | የትረካ ስልት እወዳለሁ፣ በቃ ምልልስ የተሞሉ አይነቶቹን:: አጫጫር ታሪኮችን በአጭሩ ለመቋጨት ያስችላሉ:: በየዕለቱ ለሚፈፅሙ የየቀን ሁኔታዎችን ፣ አዘቦቶች እና የተለመዱ ክስተቶችን ለመፃፍ፡፡ አንዱን ከአንዱ መደበላላቅ እና እዲስ ነገር መፍጠርም እወዳለሁ፡፡ | 它們蠻像短篇故事的,而且大多數都是有關每天發生的事,換句話說,它們會是比較平庸或平常的。 我的文章裡也會出現一些幽默的、哲學的或是能讓人自我反省的元素。 |
13 | | 我喜歡把他們混在一起,來發掘新的領域。 |
14 | GV: መጦመር መቼ ነበር የጀመርሽው ? | GV:你是什麼時候開始在部落格上寫文章的? 妳是為了什麼而寫? |
15 | ለምን ትፅፊያለሽ? | 我是在2010年開始寫文章的。 |
16 | ለመጦመር የወሰንኩት በ2010 ነው፡፡ መፃፍ ያረጋጋኛል፡፡ ሁሌም በፃፍኩ ቁጥር ከትከሻዬ ላይ ሽክም እንዳወረድኩ ይሰማኛል፡፡ ከምላሴም( ሳበሳ)፡፡ ለኔ መፃፍ ፈውስ ነው፡፡ | 我寫作的時候,都會感到很平靜。 每次在寫作的時候,我就會覺得我在一一把我肩上的重擔卸下,還有舌頭的(大笑)。 |
17 | GV: ፍቅር፣ የፍቅር እና ግብረ ስጋ ግንኝነት በተመለከተ ነው የምትፅፊው፡፡ እነዚህ ርዕሶች በአንጎላውያን ማህበረሰብ ዘንድ እንዴት ይታያሉ? | 對我來説,這是最好的療程。 GV:你常常寫一些有關愛、性和一些親密行為的內容。 |
18 | ነውር አይደሉም? | 請問安哥拉人是怎麼看待你的作品? |
19 | በአንጎላ ልቅ ወሲብን የተመለከቱ ስነፅሁፎችስ አሉ? | 它們會是禁忌嗎? 在安哥拉有性愛文學作品嗎? |
20 | የአንጎላ ማህበረሰብ እኔ ስለማነሳቸው ሃሳቦች የሚይዙት አቋም ወግ አጥባቂ የሚባል አይነት ነው(ከስፔን በመቀጠል አንጎላ የኔን ጦማር በጥቂቱ ከሚመለከቱ አገሮች ተርታ መመደቧ ይህንን እውነት ያረጋግጣል) በአንጎላ ብዙ ነውር ነገሮች አሉ፡፡ ጊዜው ጥንት ቢሆን ኖሮ የወግ አጥባቂነት ጥያቄ ነው እንል ነበር፣ ነገር ግን በማህበረሰባችን ውሰጥ በርካታ ለውጦች በሚካሄዱበት በአሁኑ ወቅት ነውር ለሚባለው ነገር ምንም ቦታ የለኝም፡፡ | 在安哥拉,當談起這些話題時,人們都還蠻保守的(這就可以解釋,僅次於西班牙,安哥拉人最少看我的文章)。 安哥拉有很多禁忌,以前我們會說這是保守主義的問題,但現在看到我們社會的變化,我認為沒有任何理由再有這些禁忌了。 |
21 | | 我是不清楚在安哥拉有沒有性愛文學(刊登或散布的)。 |
22 | | 我讀過最接近這個議題的文藝作品,大概是由詩人寶拉. |
23 | በአንጎላ ልቅ ወሲብን በተመለከተ የተፃፉ ስነፅሑፎችን አላውቅም(የተፃፉእና ለንባብ የበቁ) ለዚህ ሃሳብ ቅርብ የሆነ ያነበብኩት Paula Tavares ‘Ritos de Passagem' (Rites of Passage) የተሰኛ ስራ ነው፡፡ ሰዎች የአንጎላ ማህበረሰብ ለእንደኔ አይነት ፅሁፎች ዝግጁ አይደልም ሲሉ በተደጋጋሚ እሰማለሁ፡፡ እውነት ነው አንጎላዊያን ለእንደኔ አይነት ፅሑፎ ዝግጁ አይደሉም፣ ነገሮች በሚሄዱበት የአካሄድ ፍጥነት ከሆነ ደግሞ መቼም ዝግጁ አይሆኑም. . . | 韃維勒斯(Paula Tavares)寫的詩--「成人禮」。 我還蠻習慣聽到別人說安哥拉還沒準備好讀這類題材,這是真的! |
24 | | 而且以這種速度下去,我想那一天永遠不會到來。 |
25 | | GV:你可以說說身為一位住在羅安達的年輕女性是什麼樣子嗎? |
26 | | 其實這裡有太多對女性的不尊重以及歧視,所以當一位年輕女性很不簡單,我們在很多方面都會遭遇到刻板印象的限制。 |
27 | | GV:跟我們談談妳童年裡的一個回憶。 |
28 | | 我四歲的時候,我非常想讀我爸爸送我的故事書。 |
29 | | 所以在我念小學之前,我爸爸就幫我請了一位家教來教我讀書和寫字。 |
30 | GV: ወጣትሴት ሆኖ በሉዋንዳ መኖር እንዴት እንደሆነ ትነግሪናለሽ? | 那段每天背著包包去上家教的日子,到目前為止是我一生中最美麗的時刻。 GV:你會怎麼形容你們這一世代的安哥拉人? |
31 | | 我這個世代正在經歷一個巨大的轉變,不過這個世代非常有能力,充滿了夢想家和很有潛力的人。 |
32 | ቀላል ሆኖ አያውቅም፡፡ እዚህ ከፍ ያለ ማግለል እና ለሴት ልጅ ክብር አለመስጠት አለ፡፡ በመርህ ደረጃ ነፃ የወጣን ግን ማህበረሰቡ በዘልምድ ያስቀመጠልንን ሃለፊነት እንድንፈፅም የሚጠበቅብን ነፃ ያልወጣን ሴቶች ነን፡፡ | 但可惜的是,很少人意識到他們自己的潛力。 在另一方面,我們也很有競爭力,我們無法理解身邊為了同一個原因聚集在一起的人。 |
33 | GV: ስለልጅነት ትዝታሽ አጫውቺን? | 很少人知道聯合和團結這兩字的意思。 |
34 | | 我們有了更多可以接收資訊的管道,但即使如此,我們還是表現的像住在石器時代一樣。 |
35 | በአራት አመት እድሜዬ አባቴ ሚሰጠኝን የተረት መፅሐፎች ማንበብ በጣም እፈልግ ነበር፡፡አባቴ የቤት ውስጥ አስተማሪጋር ወስዶኝ ገና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከመግባቴ በፊት ማንበብና መፃፍ ቻልኩ፡፡ በጀርባዬ የደብተር ቦረርሳ ተሸክሜ ሁሌም አስተማሪዬ ጋር እመላለስ ነበር፣ እስካሁንም ድረስ እነዚህ የልጅነት ጣፍጭ የምንግዜም ትዝታዎቼ ናቸው፡፡ | 在安哥拉有一句諺語,「年輕人不愛玩,就不算是年輕人了」。 現在的年輕人都一心只想玩,但不用多說,還是會有一些特例。 |
36 | GV: በአንጎላ ያሉ የአንቺ ዘመን ትውልዶችን እንዴት ትገልጪያቸዋለሽ? | GV:你融入得了安哥拉較大的部落格圈嗎? 我認為可以。 |
37 | የኔ ዘመነኞች በታላቅ ለውጥ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ የሚችል ትውልድ ነው፣ህልም እና እምቅ ችሎታ ያላቸው፡፡ መጥፎው ነገር እምቅ ችሎታ እንዳላቸው የተረዱት ጥቂቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የኔ ትውልድ እርስ በእርሱ ተወዳዳሪ ነው ፡፡ ግን በዙሪያችን ያሉ ስዎች በአንድ አላማ ስር ሲሰባሰቡ አናይም፡፡ጥቂቶች ብቻ ናቸው ‘ህብረት' እና ‘በአንድ አላማ መትጋት' የሚሉትን ቃላት ፍቺ የሚያውቁ፡፡ ለመረጃ ቅርቦች ሆነን ሳለ ድርጊቶቻችን ግን በድንጋይ ዘመን እንደሚኖር ነው፡፡ በአንጎላ የተለመደ አባባል አለ “ወጣት ሆኖ በጭፈራ ቤት የማይጨፍር ወጣት አይደለም” የሚል፡፡ ወጣቶች ዛሬ ዛሬ መጨፈር ብቻ ነው የሚሹት ፣እርግጥ ነው ሁሉንም ወጣቶች በደፈናው በአንድ ማጠቃለሌ አይደለም፡፡ | 我在網路上有很多同儕,而且安哥拉的部落圈一直在成長。 臉書上有一個社團叫做「安哥拉部落客」,這裡是讓我們互相鼓勵,還有支持我們發行作品的地方。 |
38 | GV: በአንጎላ ባሉ የጦማሪያን ምድብ ስር ራስሽን ትመድቢያለሽ? | 這是一個讓我們交談,交換點子和經驗的地方。 |
39 | እንደዛ ነው የማስበው፡፡የበይነመረብ ጓደኞች አሉኝ፡፡ የአንጎላ ጦማሪያን “Blogueiros Angolanos” (“Angolan Bloggers”) የተባለ ፌስቡክ ገፅ እንደተከፈተ የአባላቱ ቁጥር ወዲያው ጨመረ፡፡ገፁን እርስ በእርሳችን ለመደጋገፍ እንዲሁም ስራዎቻችንን ለበለጠ አንባቢያን ለማዳረስ እንጠቀምበታለን፡፡ሃሳቦችን ልምዶችን የምንገበያይበት አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ ከአንጎላ ብቻም ሳይሆን ተጨማሪ በተለያዩ አገሮች በመላው አለም በይነ መረብ ጓደኞችአሉኝ፡፡ | 我不是只有在那邊有同儕,還有一些在其他的國家。 這是從「甜蜜的陳腔濫調」的Instagram所節錄的圖片: 「服務生,請給我一杯啤酒。」 |
40 | “- አስተናጋጅ እባክህን ቢራ? | 「我們沒有賣啤酒耶!」 |
41 | - ምንን የለንም፡፡ | 「那你們有賣失望嗎? |
42 | -ብስጭትስ አለህ? | 我想要雙份的。」 |
43 | ካለህ ሁለት ስጠኝ፡፡ | 「我們有喔,他就拿著煙坐在那裡。」 |
44 | - አለን፣በእጁ ሲጋራ ይዞ እዛጋ ተቀምጧል፡፡ | 「是那位男士嗎? 那我該如何稱呼他呢?」 |
45 | - እዛጋ ያለው ሰውዬ? | 「他叫做『愛情』。」 |
46 | | GV:跟我們談談你寫作的過程,你最大的挑戰是什麼? |
47 | | 一般來說,我會拿起我的電腦並花一個多小時寫作,然後作品就完成了。 |
48 | | 但有的時候,我會需要兩個禮拜來延伸我文章的內容,這常常讓我很挫折。 |
49 | ማን ብዬ ልጥራው? | 我最大的挑戰是讓讀者在我的文章裡找尋自我。 |
50 | ፍቅር ብለሽ ጥሪው ” | 我想我已經從一些回覆當中知道,我已經做到了。 |
51 | GV: ስለአፃፃፍ ሂደትሽ ንገሪን? | GV:你知道你的讀者群是誰嗎? |
52 | ስትፅፊ የሚያጋጥምሽ ችግሮችም ምንድን ናቸው? | 你的讀者通常對你的作品有怎麼樣的回應呢? |
53 | በአጠቃላይ የሞባይል ስልኬን አውጥቼ መፃፍ እጀምራለሁ፣ ከሁለት ስዓት በሚያንስ ጊዜ ውስጥ እጨርሳለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንድ ፅሑፍ ለማቀናበር ሁለት ሳምንት የፈጅብኛል፣ ያኔ ትክት ነው የሚያደርገኝ፡፡ ብቸኛው ባይሆንም አንዱና ዋንኛው ችግሬ አንባቢዎቼ በፁሑፌ ውስጥ ራሳቸውን እንዲያገኙ ማድረጉ ላይ ነው፡፡ይህንንም ችግሬን በሚገባ እንደተወጣሁት በሚደርሱኝ የአንባቢዎቼ ምላሽ ለማወቅ ችያለሁ፡፡ | 我可以說很多人會看我的文章,也就是說我的讀者群分布在各年齡層,也分布在不同的國家。 這是個很奇怪的現象,但根據統計顯示,最多人閱覽我的部落格的國家是美國。 |
54 | GV: አንባቢዎችሽ ማን ማን እንደሆኑ ታውቂያለሽ? | 有一些人還是透過Google翻譯來閱讀我的文章。 大多數的人都讚美我,也會給我一些建議並鼓勵我繼續保持下去。 |
55 | | 但當然還是會有一些人不喜歡我的文章,或者是誤解我的文章,像之前就有讀者還來告訴我多注意自己文章的內容。 |
56 | ስለፅሑፎችስ ሰዎች ምን ይላሉ? | GV:你未來有什麼抱負? |
57 | ብዙ ሰዎች ፅሑፌን ያነባሉ ማለት እችላለሁ፡፡ ይህንንም ስል በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በተለያዩ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ስዎችን ማለቴ ነው፡፡ እንግዳ ነገር ነው በአለማችን ከሚገኙ ሰዎች በስታትስቲክሱ መሰረት በርካታ አንባቢዎቼ የሚገኙት በአሜሪካን ነው፡፡በጉግል ትርጉም አማካኝነት በመጠቀም ፅሁፌን እንዳነበቡ የገለፁልኝም አሉ፡፡ አብዛኞቹ አንባቢዎቼ በርትቼ እንድቀጥልና እንድጠነክር ማበረታቻ ሃሳብ ይሰጡኛል፡፡ በሌላ በኩል በፍፁም ፅሑፌን የማይወዱና በተሳሳተ መንገድ የሚተረጉሙትም አሉ፡፡ ስለምፅፈው ፅሑፋ ጥንቃቄ እንድወስድ ማስጠንቀቂያ የሰጠኝ አንባቢም አለ፡፡ | 我是一個充滿夢想的人,但如果要我一一述說我的抱負的話,可能到今天都還說不完。 但其中一個抱負,也是最特別的一個,就是能成為報紙或雜誌上,專門寫crónica這類文章的女作家。 |
58 | GV: የወደፊት ትልሞችሽ ምን ምን ናቸው? | 這能實現的話一定很棒。 |
59 | ወደፊት ብዙ ህልሞች ያሉኝ ሰው ነኝ፡፡ ለወደፊት ማድረግ የምፈልጋቸው ትልሞቼን መዘርዘር ከጀመርኩ ዛሬ የምጨርስ አይመስለኝም ነገር ግን በጋዜጣ አሊያም በመፅሔት አምደኛ ሆኖ መፃፍ አንዱ ነው፡፡ አሪፍ ይሆናል፡፡ | 譯者:Veronica Lee 校對:Fenfen |